በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ለተቋሙ በጎ ፈ...

image description
- In code inforcement    0

በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ለተቋሙ በጎ ፈቃደኞች ግንዛቤ ተፈጠረ

በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ለተቋሙ በጎ ፈቃደኞች ግንዛቤ ተፈጠረ

           17/08/2017 ዓ.ም
            ** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ወንዝና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017  ከ11ዱም ክፍለ ከተማ ተወጣጡ በጎ ፈቃደኞች  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ በንግግራቸውም ባለስልጣኑ የከተማ አስተዳደሩ የኮሪደር ልማትን የመጠበቅ ፣ህጋዊ ንግድ የመፋጠር፣ ቆሻሻዎች በአግባቡ እንዲወገዱ የማድረግ ፣ የከተማን ፕላን የጠበቀ ግንባታ እንዲፈፀም የማድረግ ፣የመንግስትን መሬት የመጠበቅ እና ህጋዊ እርድ እንዲፈፀም የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ደንቡን በሚተላለፉት ላይ አስተማሪ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግረዋል።

አክለውም  የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ስራዎች ለመስራት ከበጎ ፈቃደኞች  እገዛ አይነተኛውን ሚና እንደሚጫዎት እና በጎ ፈቃደኞች በደንቡ ላይ ግንዛቤ አግኝተው በሚኖሩበት አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ደንቡን እንዲያስገነዝቡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት የግንዛቤ ማስጨበጥ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ደመረ በለጠ አማካኝነት በቀረበ ሰነድ  የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች ብክለት፣ በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ፣ መፍትሔዎች እንዲሁም የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 እና የቅጣት ሰንጠረዥ በዝርዝር ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

በመድረኩ የባለስልጣኑ የቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል ደንቡን በተላለፉ ድርጅት እና ግለሰብ ለይ ዝቅተኛው የገንዘብ ቅጣት ሁለት ሺህ ብር እስከ ከፍተኛው አንድ ሚሊዮን ብር ድረስ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደሚያስቀጣ ገልፀዋል።

የባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን በደንቡ ዙሪያ በተለያዩ አግባቦች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎችን በተደጋጋሚ መሰጠቱን እና ግንዛቤ የሚቀጥል መሆኑን  ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋረ ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments