ባለስልጣኑ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በዘጠኝ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን ገመገመ

ባለስልጣኑ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን ገመገመ

               16/08/2017 ዓ.ም
               **አዲስ አበባ**   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ቅንጅታዊ ስራዎችን ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ የባለስልጣኑ ኃላፊዎች በተገኙበት ከባለድርሻ አካላት አመራሮች ጋር በጋራ የግምገማ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በዘጠኝ ወራት   ከባለድርሻ አካላት ጋር በተፈራረመው ስምምነት መሰረት  የሰራቸውን ስራዎች በወቅቱ በመገምገም ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት በቀሪ ጊዜያት የአመቱን እቅድ ለማሳካት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ስራዎችን በጋራ መገምገም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።

ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የከተማችንና የአከባቢያችንን ውበት ማስጠበቅ ፣ የወንዝና የወንዝ ዳር ብክለትን በመከላከል ፣ የከተማችን ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ ፣ ህገወጥነትንና ደንብ ጥሰትን ለመከላከል ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተቀናጅቶ በመስራት ውጤታማ መሆን መቻሉን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በዘጠኝ ወራት በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች በጥንካሬ እና በጉድለት በሰነድ ተለይተው በባለስልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት፣ አገልግሎት አሰጣጥና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀጸላ ቀርቧል  ።

የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን በማጠናከር ወደ ቅጣት ከመገባቱ በፊት ለህብረተሰቡ ስለ ደንብ ማስከበር በቂ እውቀት በማስገንዘብ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር ከተማችን እንደ ስሟ አዲስና ውብ ለነዋሪዎች ምቹ ለቱሪስት መስብ እንድትሆን በትጋት መስራት እንደሚገባ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተናግረዋል ።

ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በርካታ ስኬታማ ተግባራትን በማከናወንና የገጽታ ግንባታ ስራን አጠናክሮ በመስራቱ በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች እንዲቀንሱ ማድረግ መቻሉን የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ገልጸዋል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረክ መሪዎች ምላሽና አስተያየት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments