
ባለስልጣኑ የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀሙ ከማዕከሉ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ
ባለስልጣኑ የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀሙ ከማዕከሉ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ
15/08/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2017 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም የባለስልጣኑ አመራሮችና የማዕከል ዳይሬክተሮች በተገኙበት ከማዕከሉ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለሥልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ በዘጠኝ ወራት በነበረን አፈፃፀም የታዩ ጥንካሬዎች በማስቀጠል ክፍተቶችን በመለየት በበጀት በቀሪ ቀጣይ ወራቶች የመፈጸምና የማስፈፀም አቅምን በማጎልበት ውጤታማ ተግባር ማከናወን ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2017 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል ።
በሪፖርቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የደመወዝ ልዮነትና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች መስተካከል መቻሉ፣በርካታ የተቋም ግንባታ ስራዎች መሰራታቸው ፣ የባለስልጣኑ የራሱን ስቲዲዮ በመገንባት ለቀጣይ ስራዎች ዝድጁ ማድረግ መቻሉ ፣የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፋት መስራት እና በከተማዋ የሚታዪ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ጠቅሰዋል፡፡
ባለስልጣኑ ከተሰጠው ተልዕኮ ጎን ለጎን የበጎ ፍቃድና ሰው ተኮር ሰራዎችን በማከናወን መቻሉ ጠቅሰው በተለይ አስራ አራት የአቅመ ደካማ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ ማስረከቡ በሪፖርቱ ተገልጿል ።
በወንዝና በወንዞች ዳርቻ ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችና እና የተወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ቀርባል።
የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ በመድረኩ ማጠቃለያ ባደረጉት ንግግር አፈፃፀሙ ከባለፈው አመት አንፃር በጣም የተሻለ በመሆኑ የተቋሞ ግንባታ ላይ የተሰሩ ሰራዎች ለአቻ ተቋማት ተሞክሮ እንደሆኑ ገልፀው ለቀጣይ ቀሪ ወራቶች የታቀዱት ተግባራት እንዲሳኩ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየት በማንሳት ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments