
ባለስልጣኑ በተሰጠው ሀላፊነት መሠረት የከተማው ኮሪደር መሠረተ-ልማት ጥበቃው አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ
ባለስልጣኑ በተሰጠው ሀላፊነት መሠረት የከተማው ኮሪደር መሠረተ-ልማት ጥበቃው አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ
12/08/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ በሚሠራው የልማት ኮሪደር መሰረተ ልማቶችና በመሰራት ላይ ያለው ሥራ የጥበቃ ሥራው አጠናክሮ እንደሚሠራ አስታወቀ ።
ባለስልጣኑ በዛሬው በትንሳኤ በዓል እለት ከ11ዱም ክ/ከተማ የተውጣጡ 2400 የደንብ ማስከበር አመራሮችና ኦፍሠሮች በማሳተፍ በቂርቆስ፣በየካና በአራዳ ክፍለ ከተሞች የጽዳት ዘመቻ አከናውኗል።
በጽዳት ዘመቻው በካሳንቺስ የልማት ኮሪደር ካሳንቺስ፣ ሴቶች አደባባይ ፣መለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን፣ አዋሬ፣ ግቢ ገብርኤል አካባቢ ተካሂዷል።
ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት በኮሪደር ልማት ጥበቃ ላይ ለህብረተሰቡ በተለያዩ አግባቦች ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራቱ የገለጸ ሲሆን ደንብ በሚተላለፉ ግለሰቦች ላይ አስተማሪ እርምጃዎች መውሰዱን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበዓል ቤተሰባቸውን ጥለው በተሰጣቸው ሀላፊነት መሠረት በጽዳት ዘመቻው የተሳተፉ አመራሮችና ኦፍሠሮች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
አክለውም የከተማው የኮሪደር መሠረተ-ልማት ጥበቃው አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments