ባለስልጣኑ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፅ/ቤት አመራሮች...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በማስተባበር የዝቅተኛ ደምወዝ ተከፋይ ሰራተኛ ቤት ሙሉ እድሳት አደረገ

ባለስልጣኑ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በማስተባበር የዝቅተኛ ደምወዝ ተከፋይ ሰራተኛ ቤት ሙሉ እድሳት አደረገ

          ሚያዝያ  09/2017 ዓ. ም
         **** በአዲስ አበባ****

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር እና የሰላምና ፀጥታ  ጽ/ቤት በማስተባበር ለአንድ ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ሰራተኛና ሙሉ የቤት ዕድሳት በማድረግ ለፋሲካ በአል ቤቱን አስረክቧል።

በርክክቡ ስነስርዓት ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘርሁን ተፈራ ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም ሰው ከሚያሰራው ሰራተኛ ጀምሮ ያለበትን የኑሮ ደረጃ በማየትና በመለየት መተጋገዝ፣ አብሮ መቆምና መመረዳዳት እንዳለበት አንስተው ወጣት እሸቱ የነበረበት የኑሮ ሁኔታ ከባድ እንደነበር በማየት እንደዚህ አይነት እገዛ እንዲደረግለት የተባበሩ አካላትን አመስግነዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ በበኩላቸው የፓርቲያችን ብልጽግና ሀሳብ እና የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር አብይ አህመድ መልካም ጅምር የሆነውን እንደዚህ አይነት ሰዉ ተኮር ተግባር በመስራት ዜጎችን ተጠቃሚ የማድረግ ስራ ላይ ለመሰማራት እድል በማግኘታቸው እንደተደሰቱ በማንሳት እንደዚህ አይነት ተግባር በሁሉም መለመድ እንዳለበት ተናግሯል።

በመጨረሻም ቤት የታደሰለት ወጣት እሸቱ መሐመድ የቤት እድሳቱን ላስተባበሩ ሁሉ እና ስጦታ ስለተበረከተላቸው ምስጋና አቅርቧል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments