
ባለስልጣኑ የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሄደ
ባለስልጣኑ የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሄደ
09/08/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን መጪውን የትንሣኤ በዓል አስመልክቶ ለማዕከሉ ሰራተኞችና ለሚያሳድጋቸው ህጻናት የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል ።
በማዕድ ማጋራቱ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አንድነታችንን በመደጋገፍና በመረዳዳት በተግባር በማሳየት በተለይ በዓላቶችን በሚከበሩበት ወቅት ማዕድ በማጋራት አብሮነታችን ማጠናከር አለብን በማለት ተናግረዋል፡
አክለውም አብሮነታችንን አንድነታችንን ለማጠናከር እንዲህ አይነት ኢትዮጵያዊ እሴቶችን አጠናክረን መቀጠል ይገባቸዋል በማለት በዓሉ የሰላም፣የደስታ እንዲሁም የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በማዕድ ማጋራት ተካፋይ የሆኑት የደንብ ማስከበር ኦፊሰር ወ/ሮ መሰረት ግርማ በህመም ምክንያት እረፍት ላይ መሆናቸው ጠቅሰው ተቋሙ በሚችለው አቅም ሁሉ ላደረገላቸው ድጋፍና በዛሬው ወቅት ለተደረገላቸው የበዓል ማዕድ ማጋራት ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
በተጨማሪም የባለስልጣኑ አመራሮች ለባለስልጣኑ ሰራተኞች የእንኳን አደረሳቹ መልእክታቸውን አስተላልፈው የሰው ተኮር ተግባራቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments