በከተማዋ በ64% የደንብ መተላለፎች እንዲቀንስ...

image description
- In code inforcement    0

በከተማዋ በ64% የደንብ መተላለፎች እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ

በከተማዋ በ64% የደንብ መተላለፎች  እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ

           ሚያዚያ 08/2017 ዓ.ም
          ****አዲስ አበባ****    

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር በሳሬም ሆቴል የግምገማ መድረክ አካሂዷል ። 

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ ከተማችን እንደ ስሟ አዲስ ውብ ለነዋሪዎቿ ምቹ የቱሪስት መስህብ እንድትሆን እየሰራ መሆኑ ገልፀዋል።

አያይዘውም በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በመከላከል ደንብ በማስከበርና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል። 

ባለስልጣኑ በዘጠኝ ወራት ውስጥ በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች በ64% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉንና በሰው ተኮር ተግባራት ላይ በመሳተፍ ከ የ14 የአቅመ ደካማ ቤት እድሳትና ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ ማስረከቡን ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል። 

በሪፖርቱ ታቅደው የተፈጸሙ ክንውኖች ፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተወሰዱ መፍትሔዎች ተገልፃል። 

በ9 ወሩ ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ ከ290 ሚሊዮን ብር በላይ ለከተማው ገቢ ማስገባት መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል ። 

በመጨረሻም በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጁ አቶ ንጋቱ ደኛቸው  እና ም/ስራ አስኪያጁ ከፍያለው ታደሰ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የማጠቃለያ ንግግርና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በዋና ሰራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል ። 

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments