
ባለስልጣኑ በመንገድ ሽንት በመሽናት ደንብ ቁጥር 167/2016 የተላለፉ ግለሰቦች 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
ባለስልጣኑ በመንገድ ሽንት በመሽናት ደንብ ቁጥር 167/2016 የተላለፉ ግለሰቦች 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
07/08/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በመርካቶ እና በመሳለሚያ አካባቢ በመንገድ ሽንት በመሽናት አካባቢ በማቆሸሽ ደንብ ቁጥር 167/2016 የተላለፉ 50 ግለሰቦች እየዳዳቸው 2000 ብር በድምሩ 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን ውብና ፅዱ ለማድረግ ቀንና ማታ እየሰራ ባለበት ወቅት አንዳንድ ሀላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች የተማውን ፅዳት ሲያበላሹ ህብረተሰቡ አካባቢውን ሊጠብቅ እንደሚገባ ተገልፃል።
ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 167/2016 ላይ ለህብረተሰቡ በተለያዩ አግባቦች ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራቱ የገለጸ ሲሆን ደንብ በሚተላለፉ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments