
ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የአቅመ ደካማ ቤት በትንሣኤ ዋዜማ እርክብክብ ተካሄደ።
ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የአቅመ ደካማ ቤት በትንሣኤ ዋዜማ እርክብክብ ተካሄደ።
07/08/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በወረዳ 14 ቱሉ አጀርሳ አከባቢ ቤት ገንብቶ ለአርሶ አደር ወ/ሮ ቀጨኔ ሰንበቶ አስረከበ።
በክፍለ ከተማው ስር የሚገኙትን አስራ ሶስት የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ወረዳዎችን በማስተባበር በ120 ቀናት ውስጥ የሰው ተኮር ስራውን ማከናወን ተችሏል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስከያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በምረቃ መርኃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባለስልጣኑ ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ተልዕኮውን ከመወጣት ባሻገር ባለፉት 9ኝ ወራት ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 14 ቤቶችን መገንባትና ማደስ መቻሉን አስታውሰው ፤በቀጣይም ሌሎች ቤቶችን ለማስረከብ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በምረቃ ፕሮግራሙ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወሮ ካባ መብራቱ እንደተናገሩት የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የደንብ መተላለፍችን ከመከላከል ጎን ለጎን ሙሉ ሠራዊቱን በማስተባበር ይህን የመሰለ ሰው ተኮር ስራዎች ላይ ለሚያደርገው አስተዋጽኦ በክፍለ ከተማው ስም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ በመርኃ ግብሩ ተገኝተው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በሁሉም ክፍለ ከተማዎች ግንባር ቀደም ሆኖ የሚያበረክተው ሰው ተኮሮ ስራዎች የሚደነቁና በጎነትን የሚያፀኑ መሆናቸውን በአፅንኦት ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ አለሙ እንደገለፁት የኦፊሰሩን ስነ-መሃንዲሶች እና የአስራ ሶስቱንም ወረዳ ኃላፊና ኦፊሰሮች አሻራ ጥረት ውጤት መሆኑን እና ይህ በጎ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፤ ለአርሶ አደር ቀጨኔ የአውደ ዓመት ማዕድ አጋርተዋል።
በተያዘ ዜና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ብሄረፅጌ አከባበ ከ500ሺህ ብር በላይ በሚገመት ወጪ የ2 አቅመ ደካሞች ቤቶቾን ገንብቶ ማስረከብ የተቻለ ሲሆን በቀጣይም ይህ ሰውተኮር በጎ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጽ/ቤት ኃላፊው መቶ አለቃ ቦጋለ ገልፀዋል።
በመጨረሻም በግንባታ ሂደቱ ላይ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅ ተሰጥቷል።
ዘገባባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments