በባለፈው አንድ ወር በወንዞችና የወንዝ ዳርቻ ብ...

image description
- In code inforcement    0

በባለፈው አንድ ወር በወንዞችና የወንዝ ዳርቻ ብክለት መከላከል ላይ የተሰሩ ስራዎች ተገመገሙ።

በባለፈው አንድ ወር በወንዞችና የወንዝ ዳርቻ ብክለት መከላከል ላይ የተሰሩ ስራዎች ተገመገሙ።

             03/08/2017 ዓ.ም 
            ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ  በጋራ በመሆን በወንዝ እና የወንዞች ዳርቻ ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017  ከየካቲት 24 እስከ ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም ድረስ የተሰሩ ስራዎች የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የክ/ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት ሪፓርት ሪፓርቱ ቀርቦ ተገምግሟል።

በግምገማው ላይ ንግግር ያደረጉት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በቅንጅት የመስራት ሂደቱ ያመጣው ውጤት መልካም መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም 2,858 የሚሆኑ የብክለት ድርጊቶች ከሚፅሙት ወንጀል መታቀብ በመቻላቸው ይበል የሚያሰኝ ከፍተኛ ለውጥ መሆኑን እና  የሚለቀቁ ፍሳሾች የጉዳት መጠን  በላቭራቶሪ በመመርመር እየተሰራ  መሆኑን ገልፀዋል።

በወንዝ ዳርቻ ልማትና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ  የተሰሩ ተግባራትን አፈፃፀም ሪፖርት  በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የግንዛቤ ቡድን መሪ አቶ አንበሳው  ፈንታ ቀርቧል።

በሪፖርቱም በደንብ ቁጥር 180/2017 ዙርያ 2,354,443 የህብረተሰብ ክፍሎች  ግንዛቤ መፈጠረ መቻሉን፣2,858 ከሚፈፅሙት ወንጀል ማስተካከያ መደረጉ እና ህግን ተላልፈው በተገኙ   ድርጅቶች እና ግለሰቦችን 68,896,000 (ስልሳ ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና  ስድስት  ሺህ ብር ) የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል። 

በቀረበው አፈፃፀም ሪፖርት  ላይ  በአሰራር  ላይ ያጋጠሙ አጠቃላይ ሂደቶች   በክፍተት በታዩ እና በቀጣይም መስተካከል የሚገባቸው አሰራሮች ላይ ከቤቱ   ሀሳቦች ተንሸራሸረዋል። በዚህም የተለያዩ አስተያየት እና ጥያቄዎችን በማንሳት ሰፊ ምክክር ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ በበኩላቸው  የስራ አፈፃፀሙ በጣም ጥሩ መሆኑን ገልፀው፤ ይህም ሊመጣ የቻለው  በቅንጅት በመግባባት ስራዎች በመሰራታቸው በመሆኑ ከቀሩ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት  ይበልጥ ለውጥ እንደሚያመጣ ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ወንዞች ሲፀዱ እኔም ተሳታፊ ነበርኩ የሚል ታሪክ ነጋሪ ለመሆን ወንዞች በዋናነት የሚበክሉት በማን ነው የሚለውን በማየት በቁርጠኝነት ስራዎች በጋራ እንስራ ያሉት ደግሞ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ  ናቸው።  

በመጨረሻም በተቋማቱ የበላይ አመራሮች የቀጣይ የአሰራር አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments