
የባለስልጣኑ 6ተኛ ዙር የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና በይፋ ተጀመረ
የባለስልጣኑ 6ተኛ ዙር የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና በይፋ ተጀመረ
02/08/2017 ዓ.ም
****ይርጋለም /አፖስቶ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለ6ኛ ዙር የሚያሰለጥናቸውን ከ2000 በላይ ዕጩ የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን ፌደራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አፖስቶ ካምፓስ የወታደራዊ እና የንድፈ ሃሳብ ስልጠና የመክፈቻ ኘሮግራም አካሄደ።
በፕሮግራሙ የአዲስ አበባ የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቤሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር መስፍን አበባ ፣ የሰላምና ጸጥታ እና የደንብ ማስከበር የክ/ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቤሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የከተማውን ጸጥታ በማረጋገጥና የደንብ መተላለፎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራው በአግባቡ በመወጣት ለዜጎቿና ለእንግዶቿ ምቹ እንድትሆን በርካታ ስራዎች የተሰሩና ውጤት የተገኘ መሆኑ ገልጸዋል ።
ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ ተግባራትን በዘላቂነት ለመከላከል ይቻል ዘንድ ቴክኖሎጂን ዘመናዊ መንገድ በመጠቀም የሚችል ደንብ ማስከበር ኦፊሰርን ለማብቃት መሉ ዝግጅት ተደርጎ በዛሬው ዕለት ስልጠናውን መጀመሩን በማብሰር መልካም የስልጠና ቆይታ ተመኝተዋል ።
ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2003 ተቋቁሞ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል የተቋቋመ ሲሆን አሁን ላይ ራሱን በማዘመንና ሪፎርም በማድረግ 6ኛ ዙር የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለማስልጠንና በከተማችን የሚስተዋሉትን የደንብ መተላለፎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ስልጠናውን በዛሬው ዕለት በይፋ መጀመሩን የባለሥልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልጸዋል ።
አክለውም ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የከተማውን ሰላምና ጸጥታ እያስጠበቀ ይገኛል አንዲሁም በተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎችን በመስራት ፣ የአረንጓዴ አሻራ ላይ በመሳተፍ የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር መስፍን አበበ እንደገለፁት በከተማ ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች ሰላማዊ እንዲሆንና በከተማዋ ያሉ የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል የኦፊሰሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል ።
ፕሬዝዳንቱ ስልጠናው ህጎችንና ደንቡ ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ፣ በአካል ብቃት እንዲዳብሩ፣ የህግ የበላይነት እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ የመስክና የክፍል ውስጥ ስልጠና በመሰጠት እጩ ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ውጤታማና ብቁ ሆኖ እንዲወጡ ዩኒቨርስቲው የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጸዋል ።
ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments