
ስልጠናውን በተደራጀ መልኩ ለመስጠት አስፈላጊውን ሎጀስቲክ እየተሟላ ነው" ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን የባለስልጣኑ የ6ኛ ዙር ፓራሚሊተሪ ስልጠና አስተባባሪ
"ስልጠናውን በተደራጀ መልኩ ለመስጠት አስፈላጊውን ሎጀስቲክ እየተሟላ ነው" ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን የባለስልጣኑ የ6ኛ ዙር ፓራሚሊተሪ ስልጠና አስተባባሪ
መጋቢት 29/2017
****ይርጋለም/አፖስቶ/****
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አፖስቶ ካምፓስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የገቡት የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለልጣን 6ኛ ዙር እጩ ሰልጣኞች የኮሌጁ መተዳደሪያ ህገ-ደንብ የኮሌጁ አመራሮች በተገኙበት ገለፃ ተደርጓል።
ገለፃው በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አፖስቶ ካምፓስ ኃላፊ ተወካይ ም/ኮማንደር ቦጋለ መሀመድ በአጠቃላይ በሶስቱ ቀናት ሰልጠኞችን በመቀበል ማረፊያ እና አጠቃላይ ሎጂስቲክ ለማሟላት ጥረት መደረጉ ጠቁመዋል።
አክለውም በተለይ በቀጣይ ለሚሰጠው ስልጠና በመጀመሪያ ስለጊቢው መተዳደሪያ ደንብና ህግ ማወቅ ስለሚገባ የማስገንዘብ ስራው መሠራቱ ገልጸዋል።
የባለስልጣኑ የስልጠና አስተባባሪ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን በበኩላቸው ሰልጣኞች ከሚያስፈልጉ ግብኣቶች ከመሟላት አንስቶ ሰልጣኞችን በሻለቃ፣ በሻምበል፣ በጋንታ እና በቲም የማደራጀት ተግባራትን የማከናወን ስራ እንደተሰራ በማንሳት በሚቀጥሉት የስልጠና ቀናትም ሌሎች ግባቶች በሟሟላ ስልጠናው ተደራጀ ሁኔታ በእንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የኮሌጁ መተዳደሪያ ህገ-ደንብ የተመለከተ ሰነድና ማብራሪያ በዋና ኢንስፔክተር አድማሱ በዝርዝር ቀርቧል።
ሰልጣኞችም የሶስት ቀን የነበራቸው ቆይታ መልካም እንደሆነ በመግለጽ ከስልጠናውም በኋላ የሚጣልባቸው ኃላፊነት በስነምግባር ፣ሀላፊነት ብቁ የሆነ ፓራሚሊተሪ ኦፊሰር ለመሆን ስልጠናውን እንደሚከታተሉ ገልጸዋል።
በእለቱ ከሰዓት በኋላ የሰልጣኞች የተክለ ሰውነትና የአካል ብቃት ፍተሻ በማስጀመር ለቀጣይ ስልጠናዎች ዝግጁ የማደረግ ተግባራት ተከናውኗል።
ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments