የባለሥልጣኑ 6ኛ ዙር ዕጩ ፓራ-ሚሊተሪምልምል ኦ...

image description
- In code inforcement    0

የባለሥልጣኑ 6ኛ ዙር ዕጩ ፓራ-ሚሊተሪምልምል ኦፊሰሮችን ወደ አፖስቶ የፌደራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ሽኝት ተደረገ

የባለሥልጣኑ 6ኛ ዙር ዕጩ ፓራ-ሚሊተሪምልምል ኦፊሰሮችን ወደ አፖስቶ የፌደራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ሽኝት ተደረገ

           27-07 -2017 ዓ.ም
           ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ለ6ኛ ዙር የመለመላቸው ከ2000 በላይ ሰልጣኝ ዕጩ የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በሲዳማ ክልል በሚገኘው አፖስቶ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ለማስገባት በዛሬው እለት የባለስልጣኑ እና የፌደራል ፖሊስ አመራሮች በተገኙበት ሽኝት ተደረገ። 

በሽንት ፕሮግራሙ የተገኙት የባለ ስልጣኑ ዋና-ስራአስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት በከተማው የደንብ መተላለፎች ለመቀነስና የተጀመረው የልማት ስራዎች ደህንነት ጥበቃው ለማጠናከር ተጨማሪ የሰው ሀይል በማስፈለጉ እንደሆነ ገልፀዋል።

በስልጠናው ከ11 ክፍለ ከተሞች የተመለመሉ ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው የአካልና የጤና ምርመራ በማድረግ በምልመላው ያለፉ መሆናቸው ተገልጿል 

በስድስተኛ ዙር  ዕጩ የፓራ ሚሊተሪ አዲስ ሰልጣኞችን   የንድፈ ሀሳብ  እና በወታደራዊ ሥልጠናው ከ2 ወር በላይ እንደሚቆዩ ተገልጿል ።

መረጃው፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments