የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ከድሬዳዋ ከ...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበርና ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የልምድ ልውውጥ አካሄደ

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበርና ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የልምድ ልውውጥ አካሄደ

         መጋቢት 25/2017 ዓ.ም
          **** ድሬዳዋ****
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተመራ የልዑካን ቡድን አባላት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበርና ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄደ። 

በልምድ ልውውጡ በተቋም አደረጃጀት፣ በኮሪደር ልማት ደህንነት አጠባበቅ አሰራር፣የፀጥታና የግጭት አፈታት ፤ የደንብ መተላለፎች ግንዛቤና የቁጥጥር ስራዎች፣ በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ  አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ከተማ አስተዳደሩ ያለውን ልምድና ተሞክሮው አጋርቷል፡፡

በልምድ ልውውጡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና-ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተቋሙ አደረጃጀት እና ያጋጠሙ ችግሮች ከሚመለከተው አካል በመነጋገር የተፈታበት ሂደት እና ተቋሙ በማጠናከር የከተማዋን ገጽታ በመቀየር ሂደቶች ገልፀዋል።

በልምድ ልውውጡ የባለስልጣኑ  አሰራሮች እና የተቋሙ ተሞክሮዎች  የቀረበ ሲሆን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር  ከተቋሙ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ  ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡

በልምድ ልውውጡ የሁለቱም ከተማ አስተዳደር ተቋማት የስራ ተሞክሮ በሰነድ ቀርቦ ከአመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ተቋሙ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመነጋገር እየሰራ ያለው ውጤታማ ስራዎች አድንቀው የወሰዱት ተሞክሮ ጠቃሚ እና ልምዱን በከተማው ተግባራዊ በማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

በልምድ ልውውጡ የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ፣ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም አህመድ፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ  ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።

ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments