የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ለተቋማዊ የ...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ለተቋማዊ የስራ ልምድ እና ተሞክሮ ለመውሰድ ድሬዳዋ ከተማ ገቡ

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ለተቋማዊ የስራ ልምድ እና ተሞክሮ ለመውሰድ ድሬዳዋ ከተማ ገቡ

         መጋቢት 25/2017 ዓ.ም
          **** ድሬዳዋ****
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የልዑካን ቡድን አባላት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የባለስልጣኑና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የሚሳተፉበት  የልዑካን ቡድን አባላት ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገብተዋል።

በልምድ ልውውጡ በተቋም አደረጃጀት፣ በኮሪደር ልማት ደህንነት አጠባበቅቅ አሰራር፣ ፤በሌሎች የደንብ መተላለፎችና የፀጥታ ጉዳዮች እና ከባለድርሻ  አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ከተማ አስተዳደሩ ያለውን ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት ይሆናል፡፡

በልምድ ልውውጡ የአዲስ አበባ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ዋና-ስራ አስኪያጅ ቃለቃ ዘሪሁን ተፈራ እና የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና የባለስልጣኑ አመራሮችና ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ፣ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም አህመድ፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ  ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ጀማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments