
ባለስልጣኑ ያልተጣራ ፍሳሽ በመልቀቅ ወንዝን የበከሉ ሁለት ተቋማት እያንዳንዳቸው 1,000,000 ብር በመቅጣት እርምጃ መውሰዱን ገለፀ
ባለስልጣኑ ያልተጣራ ፍሳሽ በመልቀቅ ወንዝን የበከሉ ሁለት ተቋማት እያንዳንዳቸው 1,000,000 ብር በመቅጣት እርምጃ መውሰዱን ገለፀ
24/07/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በልደታ ክ/ከተማ 2 ፍሳሽን ወደ ወንዝን በመልቀቅ ወንዝ የበከሉ ሁለት ተቋማት እያንዳንዳቸው 1,000,000 ብር በድምሩ 2,000,000/ሁለት ሚሊዮን ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ገለፀ።
ባለስልጣኑ ቢጂ አይ ኢትዮጲያ እና ሞሀ የለስላሳ መጠጦች ማምረቻ ድርጅቶች የሚለቁት ፍሳሽ በተደረገለት የናሙና ምርመራ ወንዝን የሚበክል መሆኑን የተረጋገጠ ሲሆን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
ወንዞችን ከብክለት የፀዱ ከማድረግ አንፃር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በጋራ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን በስፋት እየሰጡ መሆኑ ገልፀዋል።
በግንዛቤው መሠረት ተቋማትና ግለሰቦች ከህገወጥ ተግባራቸው ሊቆጠቡ ባለመቻላቸው አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተመላክቷል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
ዌብሳይት ገፃችን፦
https://www.aacea.gov.et/
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments