
ባለስልጣኑ የወንዞችና የወንዞች ዳርቻ ብክለት ለመከላከል የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 አፈጻጸምን ገመገመ
ባለስልጣኑ የወንዞችና የወንዞች ዳርቻ ብክለት ለመከላከል የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 አፈጻጸምን ገመገመ
23/07/2027ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በጋራ በመሆን የወንዞችና የወንዞች ዳርቻ ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 አፈጻጸም የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የክ/ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት አፈጻጸም ሪፓርት በማቅረብ አፈጻጸሙን ገመገመ።
በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በቅንጅት የመስራት ሂደቱ ያመጣው ውጤት መልካም መሆኑን ጠቅሰው ሪፖርቱን በመጠምገም በቀጣይ በትኩረት መሰራት በሚገባቸው ነጥቦች ግብአት ለመውሰድ መሆኑ ገልፀዋል።
በመድረኩ የወንዝ ዳርቻ ልማትና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ በሳምንት ውስጥ የተሰሩ ተግባራትን አፈፃፀም ሪፖርት ሰነድ በባለስልጣኑ የቁጥጥር እና ኢንሰፔክሽን ባለሙያ አቶ አባትነህ ውባለ ቀርቧል።
በቀረበው አፈፃፀም ሪፖርት ሰነድ መሠረት ከቤቱ በክፍተት በታዩ እና በቀጣይም መስተካከል የሚገባቸውና ፣ ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው ነጥቦች ላይ ሀሳብ፣ አስተያየት እና ጥያቄዎችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ የአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ ደንቡን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር የተሄደበት መንገድ ከተጠበቀው በላይ መሆኑን በመግለጽ ጠንካራውን ጎን የበለጠ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።
አክለውም በቀጣይም ግንዛቤ የማስጨበጥ እና ከሌሎች ከቀሩ ተቋማት ጋር በቅንጅት የመስራት ሂደት ላይ አሁንም ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱ መቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በተቋማቱ የበላይ አመራሮች የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments