
በስነ-ምግባር የታነፀ አመራርና ባለሙያ ለሁለንተናዊ እድገት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተገለፀ
በስነ-ምግባር የታነፀ አመራርና ባለሙያ ለሁለንተናዊ እድገት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተገለፀ
መጋቢት 23/2017
****የአዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እና ለወረዳ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት በስነ-ምግባር፣ መልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ 12 ወረዳዎች ለተወጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።
የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ኢትቻ በመረሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በስነ-ምግባር የታነፀ አመራርና ባለሙያ ለአንድ አገር ሁለንተናዊ እድገት መምጣት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
አክለውም ሰልጣኞችም ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር በተሰማሩባት የሙያ ዘርፍ አገርንና ህዝብን በቅንነትና በታማኝነት ሊያገለግሉ ይገባል ብለዋል።
ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ሰጥተዋል።
የስልጠናው ዋና ዓላማ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በሙያዊ ስነ-ምግባር ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ኑሯቸው ተግባራትን በእውቀትና በክህሎት እንዲመሩ ለማስቻል ታስቦ የተሰጠ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments