
ባለስላጣኑ በደንብ ቁጥር 179/2017 እና በደንብ ቁጥር 180/2017 ዙርያ ስልጠና ሰጠ
ባለስላጣኑ በደንብ ቁጥር 179/2017 እና በደንብ ቁጥር 180/2017 ዙርያ ስልጠና ሰጠ
መጋቢት 22/2017ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰው ኃይል ስምሪት በልዩ ሁኔታ ለማመጣጠን የወጣ የዝውውርና ምደባ ደንብ ቁጥር 179/2017 እና በወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል የወጣውን በደንብ ቁጥር 180/2017 ዙርያ ከማዕከል እስከ ወረዳ ላሉ ሰራተኞች በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የስልጠናው ዓላማ በወንዝ ዳርቻ ብክለትና እንክብካቤ የወጣውን ደንብ ሀሉም ሰራተኞች በመገንዘብ ለከተማው ህዝብ ያለውን ፋይዳ ተደራሽ ለማድረግ እንዲያስችል እና የሰው ኃይል ውስንነት ያለባቸው ቦታዎችን ተመጣጣኝ የሰው ኃይል እንዲኖራቸው ለማድረግ የወጣውን ደንብ ለይ የሚሰጠውን ስልጠና መሆኑ ገልፀው ሰለጣኞች በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል ፡፡
በወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል የወጣውን ደንብ ቁጥር 180/2017 ዙርያ የተዘጋጀ ሰነድ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠና ዳይሬክቶሬት የስልጠና ባለሙያ በአቶ ዮናኤል ለታ አቅርበዋል ።
በሰነዱ የወንዞችና የወንዞች ዳርቻን ስለማልማት፣ወንዝና የወንዝ ዳርቻ ከብክለት ስለመከላከል ፣ስለ ተከለከሉ ተግባራት ፣ ስለ ወንዝና ወንዝ ዳርቻ አስተዳደራዊ ቅጣት በሰፊው ገለፃ ተደርጓል
በሌላ መልኩ የሰው ሀይል ስምሪትን በልዮ ሀኔታ ለማመጣጠን የወጣውን ደንብ ቁጥር 179/2017 ስልጠና የሰጡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሰው ሀይል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ ሲሆኑ በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰው ሃብት ስምሪቱን ለማመጣጠን እንዲቻል የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰው ሀብት መረጃዎችን ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
በስልጠናው ከመቶ ስልሳ ፐርሰንት በላይ የሰው ኃይል ከተሟላላቸው ላይ ዝቅተኛ የሰው ኃይል ቁጥር ወዳላቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች በልዩ ሁኔታ በማዛወር ወይም በመመደብ የተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር በማስቻል የተገልጋዩን እርካታ ከፍ ማድረግ እንዲያስችል ደንቡ መደንገጉን አስገንዝበዋል ።
በለስልጠናው ሰለ ደንቡ ጠቅላላ ድንጋጌ፣ ስለ ዝውውርና ምደባ አፈጻጸም፣ ስለ አብይ ኮሚቴ አባላት እና ተግባርና ኃላፊነት፣ በዝውውር አፈጻጸም የሠራተኛ መብቶችንና ግዴታዎች ጨምሮ ዝርዝር ጉዳዮችን ላይ ሰፋ ባለ አቀራረብ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ከመድረኩ በሁለቱም ደንብ ቁጥሮች ዙርያ በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በአሰልጣኞቹ ምላሽ ተሰጥቶበት ስልጠናው ተጠናቋል።
ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments