
ለደረቅ ቆሻሻ ሽርክና ጽዳት ማህበራት በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ::
ለደረቅ ቆሻሻ ሽርክና ጽዳት ማህበራት በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ::
16/07 /2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለደረቅ ቆሻሻ ሽርክና ጽዳት ማህበራት አመራሮች የወንዝ ዳር ብክለትን ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በባለስልጣኑ አዳራሽ ለሁለት ቀናት ተካሂዷል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ እና ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ለህብረተሰቡና ማህበራት በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ከተማዋን ፅዱ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ህብረተሰቡም የከተማዋን ፅዳት በመጠበቅና የደንብ መተላለፎች ሲመለከት በማውገዝ ከተቋሙ ጎን ሊሰለፍ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች ብክለት በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እና መፍትሔዎች እንዲሁም የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል የተደነገገው ደንብ ቁጥር 180/2017 እንዲሁም የቅጣት ሰንጠረዥ በባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ኢንስፔክሽን ባለሙያ አቶ ናታን ታዬ በዝርዝር ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሮበታል።
ህብረተሰቡ ወንዞችን እና የወንዝ ዳርቻ ብክለትን ለመከላከል የወጣውን ደንብ በመገንዘብ በየአካባቢው የሚገኙ ወንዞችን ከብክለት በመጠበቅ የእራሱን እና የሌሎችን ጤና ማስጠበቅ እንደሚገባ የደንብ መተላለፍ መከላከልና የግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን አብራርተዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments