
ስነምግባር በተላበሰ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ
ስነምግባር በተላበሰ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ
12/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ለአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች "ስነ-ምግባርና መልካም አስተዳደር ለተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ" በሚል መሪ ቃል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በክ/ከተማው አዳራሽ ሰጠ።
ስልጠናውን የሰጡት የባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ የስነምግባርና ብልሹ አሰራር ችግር ለተቋማችን ገጽታ ግንባታ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በመገንዘብ በዚህ ድርጊት በሚሳተፉ ላይ ጠንካራ የተጠያቂነት ስርዓት በመዘርጋትና በመከላከል ሁሉም አካል ብልሹ አሰራርን ሊጸየፍና ሊታገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ስነ-ምግባር ለመልካም አስተዳደር መስፈን ያለዉ ፋይዳ የላቀ በመሆኑ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለሌሎች አርኣያ የሚሆን ስነ ምግባር በተላበሰ መልኩ አገልግሎቶችን መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አቶ እዮብ ገልጸዋል ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን ኦፊሰሩ ከብልሹ አሠራር እራሱን በመጠበቅ የተሰጠዉን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣትና ከዳር ማድረስ እንዳለበት ገልጸዋል።
በመድረኩም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments