
ሕብረተሰቡ የተቋሙን ስም ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ ህገ-ወጦችን እንዲያወግዝ ጥሪ ቀረበ
ሕብረተሰቡ የተቋሙን ስም ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ ህገ-ወጦችን እንዲያወግዝ ጥሪ ቀረበ
12/07/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልኮ ለማስፈፀም ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ተጨባጭ የሆነ ለውጥን በማስመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡
ባለስልጣኑ ለህብረተሰቡ ጥቅም ሲባል የሚወጡ ደንቦችን አስቀድሞ ግንዛቤ እያስጨበጠ፤ ሆን ብሎ ደንቡን ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም አካል ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን በመውሰድ የደንብ መተላለፍን በመከላከል ላይ ይገኛል፡፡
በዛሬውም ዕለት የተቋሙ ያልሆነ የደንብ ልብስ በመልበስ የሱቅ ማስታወቂያ ሰርተው በማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጩ ተጠርጣሪ ግለሰቦችን የአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ ተጨማሪ ምርመራ እያካሄደ በመሆኑ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ታላቅ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
ሆኖም ተጠርጣሪዎቹ የለበሱት ዩኒፎርም የቀድሞውንም ሆነ የአሁኑን የተቋሙን የደንብ ልብስና ሎጎ የማይወክል መሆኑን ባለስልጣኑ ያስታውቃል፡፡
ህብረተሰቡም ማንኛውም የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ደንብ አስከባሪ የሆነ ኦፊሰር የተቋሙን ሎጎ ያለበት ዪኒፎርም በመልበስ ደንብ የሚያስከብር መሆኑን በመገንዘብ ህገ ወጥ ግለሰቦች ከሚያደርጉት ማጭበርበር እራሱን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፏል።
ባለስልጣኑ ሕብረተሰቡ የተቋሙን ስም ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ ህገ-ወጦችን እንዲያወግዝ ጥሪ የቀረበ ሲሆን ማንኛውም የሚያጠራጥር ጉዳይ ሲያጋጥመው በ9995 ነፃ የስልክ መስመር እና በክፍለ ከተማና ወረዳ በሚገኝ መዋቅር የደንብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
ዌብሳይት ገፃችን፦
https://www.aacea.gov.et/
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments