ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሲ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የ6ኛ ዙር ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአሰልጣኞች ስልጠና አጠናቀቀ።

ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የ6ኛ ዙር ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአሰልጣኞች ስልጠና አጠናቀቀ።

                            
                   11/07/2017 ዓ.ም
                    ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቀጣይ ለሚሰጠው 6ኛ ዙር የፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና የባለድርሻ አካላት ደንብ፣ መመሪያና አሠራርን የተመለከቱ ንድፈ ሀሳቦች ላይ ሲሰጥ የቆየው የአሠልጣኞች ስልጠና በዛሬው እለት አጠናቋል። 

ባለስልጣኑ  ከግንባታ ፍቃድ፣ መሬት አስተዳደር ፣ ከተማ ግብርና፣ ቄራዎች ድርጅት፣ አከባቢ ጥበቃ፣ ውኃና ፍሳሽ፣ ፅዳት አስተዳደር፣ ትራፊክ ማናጅመንት፣ ንግድ ቢሮ፣ ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን እና የገቢ ደረሰኞች የውስጥ ቁጥጥር ኦዲት ጋር በጋራ በመሆን ከማዕከል እና ከአስራ አንዱም ክ/ከተማ ለተውጣጡ ሰልጣኞች በማዕከሉ አዳራሽ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ስልጠናውን ሲሰጥ ቆይቷል።

የስልጠናና ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላቀች ኃይሌ እንደተናገሩት ሰልጣኞች የስልጠናውን ዓላማ በመረዳት ያገኙትን እውቀት የተሻለ አፈጻጸም እና ትግበራ ላይ እንዲውል ለማስቻል በቀጣይ በሚሰጡት ስልጠና ላይ አጽኖት በመስጠት እና በማስገንዘብ ሀላፊነት መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ በቆየው ስልጠና ላይ ባለድርሻ ተቋማቱ በነባር እና በተሻሻሉ ደንብ ፣ መመሪያዎች እና አሰራሮቻቸው ላይ ከደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ጋር በመሆን በቀጣይ ከህግ አንጻር በቅንጅት እንሰራበታለን ባሏቸው ነጥቦች ላይ ሰነዶችን አቅርበዋል። 

በስልጠናው ሂደት ላይ ከሰልጣኝ ኦፊሰሮች ሊነሱ ይችላሉ ባሏቸው ነጥቦች እና አጠቃላይ በነበሩ ቀናት ባይዋቸው ሰነዶች ላይ ከቤቱ ጥያቄዎች በማንሳት ከተቋማቱ በመጡ ተወካዮች ከመድረክ ምላሸ በመስጠት የጋራ ተደርጓል።

በመድረኩ ማጠቃለያ የሰጡት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የስልጠናውን ዓላማ በመረዳት ለቀጣይ በማንኛውም የስራ ተልዕኮ እና መደበኛ ስራ ዘላቂነት የበኩላቹን ድርሻ መወጣት እንደሚገባም በማሳሰብ ሰልጣኞች በዲስፕሊንና በመልካም ተሳትፎ ስልጠናውን ስለተከታተሉ በማመስገን በቀጣይ የበለጠ ለቅንጅታዊ አሰራር ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንደሚገባ እና ሰለጣኞችንም በሚፈለገው ልክ ብቁ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ዘገባው:- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments