ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የስራ አፈጻጸም...

image description
- In code inforcement    0

ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ።

ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ። 

                   11/07/2017 ዓ.ም
                  ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ወንዞችና የወንዝ ዳርቻዎችን ብክለት መከላከል ላይ የተከናወኑ ተግባራትን የስራ አፈጻጸም ግምገማ የተቋማቱ አመራሮች በተገኙበት በደንብ ማስከበር ባለስልጣን አዳራሽ አካሂዷል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት በቅንጅት ስራዎችን በማከናወን የተሻለ የስራ ባህልን ማዳበር እና ውጤታማ መሆን ተችሏል ብለዋል።

በቀጣይም አያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመፍታት ከተማችንን ጽዱ ውብ እና ህገወጥነት የቀነሰባት ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል። 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ወንዞችና የወንዝ ዳርቻዎችን ብክለት መከላከል ላይ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት በአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የአከባቢ ትምህርትና ግንዛቤ ቡድን መሪ አቶ አንበሳው ፈንታ ቀርቧል።

በሪፖርቱም በደንብ ቁጥር 180/2017 የተፈጠሩ ግንዛቤዎችና ህግን ተላልፈው በተገኙ አካላት ላይ የተላለፉ 282 ድርጅቶች እና ግለሰቦችን 58,161,000(ሀምሳ ስምንት ሚሊዮን መቶ ስልሳ አንድ ሺ ብር ) የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል። 

በመድረኩ የአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት እና የአከባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊዎች የስራ አፈጻጸም ክንውኖች፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተከናወኑ መፍትሔዎችን ተገልፀዋል። 

ለህብረተሰቡ በቂ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን በመስጠት ወንዞችንና የወንዝ ዳርቻ ጽዱ ማድረግ ለከተማውና ለነዋሪዎች ውብና ማራኪ አካባቢን  የሚያጎናፅፍ መሆኑን አንዲገነዘብ በማድረግ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የበኩልን ሀላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ ተናግረዋል። 

አክለውም ደንቡን ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል። 

ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ እንደተናገሩት ለወንዝ ብክለት መንስኤዎችን ምንድናቸው የሚለውን በመለየትና ጥናቶችን በማጥናት እንዲሁም ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር የወንዝና የወንዝ ዳር አከባቢ ብክለቶችን በመከላከልና በመቆጣጠር የህግ የበላይነት ማስከበር ይገባል ብለዋል። 

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments