
ባለስልጣኑ ወንዝን በመበከል ከድርጊታቸው ያልተቆጠቡ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን 5,910,000/ አምስት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ አስር ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
ባለስልጣኑ ወንዝን በመበከል ከድርጊታቸው ያልተቆጠቡ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን 5,910,000/ አምስት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ አስር ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
10/07/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት 5,910,000/ አምስት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ አስር ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 2,100,000 ብር፤በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 910,000 ብር ፤ በኮልፌ ክፍለ ከተማ 690,000 ብር፤በየካ ክ/ከተማ 600,000 ብር ቅጣት ቀጥቷል።
በያያዘ ዜና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር ፤በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር እና በልደታ ክ/ከተማ 400,000 ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ተደርጓል።
በአጠቃላይ በዛሬው እለት 17 ድርጅት እና
8 ግለሰቦች በድምሩ 5,910,000/ አምስት ሚሊየን ዘጠኝ መቶ አስር ሺህ/ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።
ባለስልጣኑ በተሰጠው ግንዛቤ መሠረት ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ በመበከል ከድርጊታቸው ያልተቆጠቡ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments