ባለስልጣኑ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ በሚበክሉ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ በሚበክሉ አካላት ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉን ገለጸ

ባለስልጣኑ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ በሚበክሉ አካላት ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉን ገለጸ      
        
                 04/07/2017 ዓ.ም
             ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር  ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን  በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት በዛሬው እለት 5,775,000/አምስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሰባ አምስት ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት  በመቅጣት  አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 1,595,000 ብር፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 1,150,000 ብር፣በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 1,050,000 ብር ፤በአራዳ ክፍለ ከተማ 650,000 ብር፣አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 640,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

በተያያዘ ዜና በቦሌ ክ/ከተማ 300,000 ብር ፤በአቃቂ ክ/ከተማ 300,000 ብር በልደታ ክፍለ ከተማ 70,000 ብር ፣በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ 20,000 ብር በመቅጣት  አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

ባለስልጣኑ በአጠቃላይ በዛሬው እለት 27 ድርጅቶች እና 15 ግለሰቦች በመቅጣት በድምሩ 5,775,000/አምስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሰባ አምስት ሺህ/ ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ማድረጉን ገልጿል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments