ባለስልጣኑ በተሻሻለው የመንግሥት ሰራተኞች አዋጅ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በተሻሻለው የመንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ ስልጠና ሰጠ

ባለስልጣኑ በተሻሻለው የመንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ ስልጠና ሰጠ

        15/ 11/2017 ዓ.ም
        **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ ለማዕከል ሰራተኞችና ለክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ሰራተኛው አዲስ ተሻሽሎ የወጣውን የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ላይ በቂ ግንዛቤ ኖሮት መብትና ግዴታውን በማወቅ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ስራውን በተሳካ ሁኔታ እንዲያከናውን ስልጠናው መዘጋጀቱ ገልፀው ሰልጣኞች በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል ።

ስልጠናው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰው ሀብት ክትትል፣ድጋፍና ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ተመስገን በዝርዝር ከነ ማብራሪያው  ሰጥተዋል።

በስልጠናው የአዋጁ መሻሻል በመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰጡ አገልገሎቶችን ለማዘመን፣ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደርን ለማሻሻልና ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት መሆኑ አስረድተዋል።

የመንግስት ሰራተኛው በምዘና ውስጥ እንዲያልፍ በማድረግ እውቀትና ብቃት ባለው ሲቪል ሰርቫንት  በከተማዋ ውስጥ እየተመዘገበ ያለውን እድገት ለማስቀጠል እንደሚሰራ በስልጠናው ተገልጿል ።

በመጨረሻም በቀረበው የስልጠና ሰነድ ዙሪያ ከሰልጣኞች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments