ባለስልጣኑ የድምፅ እና የምስል ስቱዲዮ ገንብቶ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የድምፅ እና የምስል ስቱዲዮ ገንብቶ በማጠናቀቅ የምርቃት ፕሮግራም አካሄደ

ባለስልጣኑ የድምፅ እና የምስል ስቱዲዮ ገንብቶ በማጠናቀቅ የምርቃት ፕሮግራም አካሄደ

               05/ዐ1/2018 ዓ.ም
                **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ያስገነባውን የድምፅ እና የምስል ስቱዲዮ በማጠናቀቅ የከተማውና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የምርቃት ፕሮግራም አካሂዷል ።

በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የስቶዲዮ ግንባታው ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት በከተማችን የደንብ ጥሰት እንዳይፈጽም የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎቻችን በማጠናከር ህብረተሰቡ  ህገወጥነትን እንዲጸየፍ በሚዲያ ስራውን ለማጠናከር  መሆኑ ገልጸዋል ።

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ባደረጉት ንግግር ተቋሙ የገጽታ ግንባታ ስራውን አጠናክሮ በመስራቱ በየጊዜው የሚታይ ለውጦችን እያመጣ ይገኛል ለዚህም ቀን ከለሊት ሳይሉ የሚሰሩት የተቋሙ አመራሮች፣ ሰራተኞች እና በከተማው ያሉ ኦፊሰሮች ላቅ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል ሱሉ   ተናግረዋል።

አክለውም ጊዜው የመረጃና ኮሙኒኬሽን እንደመሆኑ የስቱዲዮ ግንባታው የመረጃ ቅብብሎሽ የሚያሳድግና ተቋሙ የሚያከናውነውን ተግባራት ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረውና አጋዣ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል በማለት በቀጠይም በሙያዊና በቴክኖሎጂ በሚያስፈልጉ ነገሮች በሚቻላቸው ድጋፍ እንደሚያደረጉ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሁሴን ዝናብ በምርቃት ፈጣንና ዘመናዊ መረጃን ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡን የተቋሙ አጋዥ በማድረግ የደንብ ጥሰት የቀነሰበት እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለመፍጠር  ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተናግረዋል ።

የስቱዲዮ ግንባታ ያስፈለገበት ምክንያት እና በቀጣይ በስቱዱዮው  የሚያከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የሚገልፅ አጭር ሰነድ በባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ አቅርበዋል ።

በመድረኩ የከተማው የተቋማት ሀላፊዎች የሚዲያ አመራሮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ተገኝተዋል።

ዘገባው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments